Asset Publisher Asset Publisher

Return to Full Page

በደብረ ብርሃን ከተማ ታህሳስ 16 እና 17 /2012 ዓ.ም. የንባብ ሳምንት ማዘጋጀቱ ተገለጸ (ታህሳስ 15 ቀን 2012 ዓ.ም)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ በደብረ ብርሃን ከተማ ታህሳስ 16 እና 17 /2012 ዓ.ም. የንባብ ሳምንት ማዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡
በዝግጅቱም፡-
 ለከተማው ትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት መመስረት አስፈላጊነት ላይ በታዋቂ ደራሲያንና የሥነ ጽሁፍ ባለሙያዎች ምክርና ግንዛቤ ይሰጣል፣ የንባብ ክበባት ይመሰረታሉ፣ የመጽሐፍት ልገሳ ይደረጋል፡፡

 የሥነ-ጽሑፍ ምሽት ለከተማ ነዋሪዎችና ወጣቶች ይካሄዳል፡- በታዋቂ ደራሲያን፣አርቲስቶችና የሥነ ጽሁፍ ባለሙያዎች ምክርና ግንዛቤ ይሰጥበታል፤ አነቃቂ ንግግሮች፣ግጥም፣ መነባንብ፣ ጭውውት እና ሌሎችም የኪነ ጥበባት ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡ ወጣቶች ክህሎታቸውን ያቀርባሉ፣ በኤጀንሲው ይሸለማሉ፤ ይበረታታሉ፡፡

 በደብረ ብርሃን ማረሚያ ቤት የንባብ ሳምንት ይካሄዳል፤ በታዋቂ ደራሲያንና የሥነ ጽሁፍ ባለሙያዎች ስለ ንባብ ጠቀሜታ ምክርና ግንዛቤ ይሰጣል፤ ለማረሚያ ቤቱ የመጽሐፍት ልገሳ ይደረጋል፡፡
በመሆኑም ይህንን ታላቅ ዝግጅት የሚድያ አካላት ቅድመ መረጃውን ለአድማጭ ተመልካች እንዲያስተላልፉ ተጠቁሟ ፣ ጥሪ የተደረገላችሁ ተሳታፊዎች፣ የሚድያ አካላትና የከተማው ነዋሪዎች በፕሮግራሙ ላይ እንድትገኙ ግባዣችንን እናቀርባለን በማለት የኤጀንሲው የህዝብ አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታዩ አስታውቀዋል፡፡